Skip to main content
x

ሕብረት ባንክ አ.ማ የባንክ አክሲዮኖች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤

 

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በበቅሎ ቤት ቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን የባንክ አክሲዮኖች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

 

የቅርንጫፍ ስም

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዦች ስም

አክሲዮኖቹ የሚገኙበት ድርጅት (አ.ማ.)

የሰርተፊኬት ቁጥር

የአክሲዮን ብዛት

የአንዱ አክሲዮን ዋጋ /በብር/

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

/በብር/

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

በቅሎ ቤት

ሳትኮን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/ የግል ማህበር

አቶ ሳሙኤል ተክላይ

አቢሲኒያ

ባንክ አ.ማ

01551

28,856

25

የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 25

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

 

የሐራጅ ደንቦች

 

1. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት በ25 አባዝተው የሚገኘው መጠን ላይ አንድ አራተኛ  በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

2. አሸናፊ የሆነዉ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸዉ፡፡

4. የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደዉ ሕብረት ባንክ አ.ማ. ዋናዉ መስሪያ ቤት ሚክዎር ህንፃ፣ ሁለተኛ ፎቅ ባለዉ የስልጠና መስጫ ክፍል /Training room/ ዉስጥ ነዉ፡፡

5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡

6. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር /የጨረታዉ አሸናፊ/ ገዥዉ ይከፍላል፡፡

7. ባንኩ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርቡ ተጫራቾች ኢትጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. አንድ ተጫራች ከላይ በሰንጠረዡ የተገለጸው የአክሲዮን ብዛት  በሙሉም ሆነ በከፊል ለመግዛት መጫረት ይችላል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ለአንድ አክሲዮን በሚቀርበው ከፍተኛ ዋጋ መሰረት ከከፍተኛው ወደ ዝቅተኛ በቀረበው ዋጋ ቅደም ተከተል ነው፡፡

11. አግባብነት ያላቸው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎች ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 465 52 26/16 85 76   በቅሎ ቤት ቅርንጫፍ ወይም 0114-70 03 15/69/47 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ማሳሰቢያ፡

  • የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም የወጣዉ የሐራጅ ማስታወቂያ በዚህ ማስታወቂያ የተተካ መሆኑን እንገልጻለን፡፡