አቢሲንያ ባንክ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ካሉ ገዢ ይከፍላል፡፡ ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ወደ አሸናፊው የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ስጪው ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ጨረታው የቀረበው ጊዜ |
1 |
ዳቪንተስ ዊንድ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
እስከ የካቲት 04 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 11,067,167.93 |
አምዳን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አ/አ ን/ስ/ላፍቶ/ክ/ከተማ ቀበሌ15 የቤት/ቁ አዲስ |
ብር 24,085,740.00 |
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
ለኢንዱስትሪ/ለፋብሪካ |
2,369 ካ.ሜ |
ኢ/ዞ/007/01/96 |
ለመጀመሪያ ጊዜ
|
2 |
ወ/ት ከድጃ አህመድ |
እስከ ግንቦት 24 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ ብር 19,922,783.24 |
አቶ አወል ሀሰን |
አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ |
ብር 12,323,350 |
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
መኖሪያ ቤት B+G+3 |
183 ካ.ሜ |
ቦሌ10/60/104-4767/292865/01 |
በድጋሚ |