Skip to main content
x

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ. በትራፊክ አደጋ ምክንያት ግጭት ደርሶባቸው ለተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ የሚሆን መሬት/ቦታ/ ግዢ ጨረታ

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

የጨረታ ቁጥር፡-001/2013

     1. ጨረታውን ያወጣው ድርጅት

                  ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

አድራሻ፡- አ.አ. ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 377 ስልክ ቁጥር 0115-53-53-00 ፋክስ 0115-50-00-55

       2. የቦታው/መሬቱ አጠቃላይ ሁኔታ

 • የቦታው ስፋት ከ3000-5000 ካ.ሜ. ስፋት ያለው መሆን አለበት፣
 • የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት /ካርታ/ ያለው መሆን አለበት፣
 • በእዳ ክልከላ እና ይግባኛል ክርክር የሌለበት መሆን አለበት፣
 • ከሳሪስ አቦ፣ ሃና ማርያም እስከ ሀይሌ ጋርመንት፣
 • ገላን ኮንደምኒየም በአዲሱ መንገድ፣ ሀይሌ ጋርመንት ጀርመን አደባባይ፣
 •  ከቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ እስከ ጃቲ ኪዳነ ምህረት፣ ወርቁ ሠፈር፣ ወሃ ልማት፣ አምባሰል መጋዘን እስከ መከላከያ ካምፕ፣
 • ከቃሊቲ ቆርቆሮ ፋብሪካ እስከ ጉስቋም ማርያም በአዲሱ አስፋልት፣ ከአቃቂ እስከ ገላን ከተማ
 • ከዋና መንገድ ብዙ የማይርቅና ወደ ቦታው ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች በክሬን እየተጎተቱና ተጭነው ለማስገባት ምቹ የሆነ መንገድ ያለው፤
 • ቦታው ላይ  ያረፈ መጋዘን ያለው
 • ቦታው ላይ መብራትና ውሃ ያለው፤
 • ከዋና አስፋልት ከ500-1000 ካሬ ሜትር ርቀት ያለው፡

 

3. የጨረታው አቀራረብ፡-

 • ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ ቦታ ያላቸውና ለመሸጥ ፍላጎት ያላቸው ግለሠቦች/ድርጅቶች/ ለዚሁ የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ከኩባንያው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 405 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 •  
 • ጨረታው ከመስከረም 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተጫራቾች ሳይገኙ ጨረታው ሊከፈት ይችላል፡፡

 

አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 377 ከኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ