Skip to main content
x

አምባስል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር /ከዚህ በኃላ ሻጭ ተብሎ ሊጠራ ይችላል/ ደረቅ የሰሊጥ ብጣሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡

 የሰሊጥ ብጣሪ ሽያጭ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፤

አምባስል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር /ከዚህ በኃላ ሻጭ ተብሎ ሊጠራ ይችላል/ ደረቅ የሰሊጥ ብጣሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛዉም የሚከተለዉን መመሪያ አሟልቶ የተገኘ ሰዉ / የተፈጥሮም ይሁን ህጋዊ ሰዉነት ያለዉ ድርጅት / በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል፡፡

1.    ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያመላክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፤

2.    የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤

3.    የንግድ መለያ ቁጥር/TIN / ያለዉና ማቅረብ የሚችል፤

4.    ማንኛዉም ተጫራች በጨረታዉ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ያቀረበዉን የመጫረቻ ዋጋ 5 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፣

5.    ማንኛዉም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤

6.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00/ አንድ መቶ/ በመክፈል በሻጭ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503፣ ጎንደር ከተማ የኩባንያዉ ቢሮ ጎንደር ፕሮሰሲንግ አገልግሎት አዘዞ፣ ባ/ዳር ጣና ክፍለ ከተማ አምባሰል ህንፃ ባ/ዳር አ/ቅ/ፍ ቢሮ፣ እና ደሴ ሆጤ ክፍለ ከተማ መናሃሪያ ወረድ ብሎ ጅንአድ የሚገኝበት ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ ደሴ አ/ቅ/ፍ ቢሮ ድረስ በመሄድ መግዛት ይችላሉ፣

7.    ጨረታዉ አየር ላይ የሚቆየዉ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ /ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፤30 እሰከ 6፤30 ያለዉ ጊዜ የሻጭ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል/ በ15ኛዎዉ የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ የሁሉም ቅርንጫፎች የመጫራቻ ሰነዶች ተሰብስበዉ 20ኛዉ ቀን ላይ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት አ/አበባ የሻጭ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602 የጨረታ መክፈት ስነ-ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፣

8.    ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-466-6328 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፣

9.    ስለ ምርቱ መረጃ ለማግኘት ጎንደር 09-18-35-00-53/058-114-0393/ መደወል የሚችሉ ሲሆን በአካል ለማየት ለሚፈልግ ጎንደር ፕሮሰሲንግ አገልግሎት ድርጀቱ መጋዘን በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡

አምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማህበር