Skip to main content
x

አክሲዮን ሽያጭ

ለዳሸን ባንክ አ.ማ  ባለአክስዮኖች

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ

የዳሸን ባንክ አክስዮን ማህበር ባለአክስዮኖች 21ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ የባንኩን ካፒታል እንዲያድግ ውሳኔ ማሳለፉን መሠረት በማድረግ የካፒታል ዕድገትን አስመልክቶ የንግድ ህጉ የቅድሚያ የግዢ መብት የሚሰጠው ለባለአክስዮኖች በመሆኑ በዚህ ውሳኔ መሰረት ባለአክስዮኖች በአክስዮን መጠናቸው የተደለደለላቸውን አክስዮን ግዥ ከሚያዚያ 01 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ እንዲያከናውኑ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን የተረፉ አክስዮኖች ስላሉ የባንኩ ባለአክስዮኖች በአክስዮን መጠናችሁ የተደለደለላችሁን ተጨማሪ አክስዮኖች ግዥ ከሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በዳሸን ባንክ አክስዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስና ሂሳብ መምሪያ በመቅረብ እንድትገዙ እናስታውቃለን፡፡

ዳሸን ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ጽ/ቤት