የጽዳት አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ NBE/NCB/S/07/2017/18
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጽዳት አገልግሎት ግዥ ለሦስት አመታት የሚያቀርብ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግብት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ተጫራቾች፡-
- በመስኩ በ2010 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታታማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም Unconditional Bank Guarantee ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ባንኩ በሚገኝበት አዲስ ህንጻ ምድር ቤት በሚገኘው ሒሳብና ክፍያ ማወራረጃ ክፍል ከሰኞ እእስከ አርብ በስራ ሰአት በሂሳብ ቁጥር 7002010800001 ገቢ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ በነባሩ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሀምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀኑ ሀምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሊገኙ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251115175225/+251115177006/7082 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡