የሬዲዮ ፕሮግራም አገልግሎት ግዥ
የአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ህግ እና አሰተዳደር ትምህርቶች ኮሌጅ
የሬዲዮ ፕሮግራም አገልግሎት ግዥ ጨረታ (በድጋሚ የወጣ)
የግዥ መለያ ቁጥር: AAU/CLGS/NCB/002/2010
1. የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህግና አስ/ትምህርቶች ኮሌጅ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ከሮያል ኖርዌይ ኢምባሲ እና ከሲዊዲን አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሚተገብረው ፕሮጀክት (Project to Support Teaching, Research and Community Engagement in Human Rights (Project STRACE-CHR) ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስመልክቶ በተለይም በሴቶች፣ በህጻናት፣ በሰራተኞች ፣ በስደተኞች እና በአካል ጉዳተኞች ሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ እንዲሁም አጠቃላይ በመሰረታዊ ህገ-መንግስታዊ መብቶች ዙሪያ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ በጨረታ ማሰራትና ማሠራጨት ይፈልጋል፡፡
2. ጨረታው የሚከናወነው በኢትዩጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የመንግስት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ይሆናል ፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም አገልግሎት ግዥ ጨረታው የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የ2010 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ፣ እንዲሁም ቲን እና ቫት ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል ፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6 (ለ) በተገለጸው አድራሻ እስከ ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም 8፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያውን በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረው መሰረት አያይዘው ያቀርባሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ጨረታው ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ስዓት ታሽጎ በዚያኑ እለት በጨረታው ላይ ለመገኘት የሚፈለጉ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 6(ሐ) በተጠቀሰው አድራሻ ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ስዓት ላይ ይከፈታል፡፡
4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 6(ሀ) በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6(ለ) በተገለጸው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታተይ ቀናት እስከ ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ስዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 6,000.00 (ስድስት ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ሀ/ ሰነዶቹ የሚገኙበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህ/አስ/ት/ኮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 017 ይሆናል፡፡
ለ/ የጨረታው ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህ/አስ/ት/ኮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 017 ይሆናል፡፡
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህ/አስ/ት/ኮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 017
7. ዩኒቨርሲቲው በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118-69-56-54/01-11-23-37-83/ በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኝት ይችላሉ ፡፡