የከባድ ተሸከርካሪዎችን ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
እንደራስ ናሽናል ኃ.የተ.የግ.ማህበር ንብረትነታቸው የትራንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የሆኑትን አምስት ከባድ ተሸከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል'
- የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም በስራ ሰዓት በአዳማ ከተማ ሶደሬ መንገድ ላይ ናዝሬት አርሲ ሳሙና አካባቢ በሚገኘው የኩባንያው ተሸከርካሪዎች ቅጥር ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡
- የትራንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ፣ በአዳማ ከተማ አሰላ መንገድ ላይ ናዝሬት አርሲ ሳሙና አካባቢ ትራንስ ማቆሚያ ቅጥር ግቢ ውስጥ፤
- ለተጫራቾች የተዘጋጀው እና የተሽከርካሪዎቹን/ንብረቶቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አዳማ በሚገኘው ትራንስ ግቢ ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከዘሪሁን ህንፃ ወረድ ብሎ ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ ኤን.ቢ ቢዝነስ ሴንተር 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል'
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን እያንዳንዱን ተሸከርካሪ / ንብረት ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፐ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከዘሪሁን ህንፃ ወረድ ብሎ ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ ኤን.ቢ ቢዝነስ ሴንተር 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል'
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ተሸከርካሪ / ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% (አርባ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) መስያዝ ይኖርባቸዋል' ለተሸነፈ ተጫራች በማስያዣነት ያስያዘው የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ተመላሽ ይደረጋል'
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ስም ከፍለው እንዲወስዱ ይደረጋል' ግዥውን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይፈቀድ መሆኑን እየገለጽን ይህ ካልሆነ ግን አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከቢሪያ (C.P.O) በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል'
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ በተናጠልና በግልጽ 15% VAT መጨመሩን ወይም አለመጨመሩን ማሳየት አለባቸው'
- ጨረታው ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በእንደራስ ናሽናል ኃ.የተ.የግ.ማህበር ዋና መ/ቤት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከዘሪሁን ህንፃ ወረድ ብሎ ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ ኤን.ቢ ቢዝነስ ሴንተር 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል'
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ / ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል' ሙሉ ክፍያ ፈጽመው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለ 15 ተከታታይ ቀናት በየቀኑ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ 15 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል'
- ለጨረታ በቀረቡት ተሸከርካሪዎች / ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል'
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935-40-11-29፣ 011-618-08-43 በመደወል ወይንም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መረዳት ይቻላል'
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው'
ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ከእንደራስ ናሽናል ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጋር በመተባበር