ለተለያዩ መኪናዎች እና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SP/83/2018
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዲንግ ፊንግ፣ የስካንያ፣ የስታየር፣ የቲዮታ 2H፣ የቲዮታ 3Y፣ የቲዮታኮሮላ፣ የካቻማሌ ወዘተ --- መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ አስመልክቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሱት ብዛት እና ስፔሲፊከሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 18/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ስኔ 18/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞ ኖሬላ ግቢ