ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት 11-10B የሚውል በግራናይት መደብ ላይ የሚቀረፅ የመከላከያ ሚኒስቴር Logo እና በተመሳሳይ የግራናይት መደብ ላይ በወርቃማ ቀለም (Golden Color) በእንግሊዘኛ እና አማርኛ የሚቀረፅ የዋና መስሪያ ቤቱን ስም የአቅርቦት እና ገጠማ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
F.D.R.E Ministry of Defense
Defense Construction Enterprise
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE ፕሮ/11-10B/14/2011
ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት 11-10B የሚውል በግራናይት መደብ ላይ የሚቀረፅ የመከላከያ ሚኒስቴር Logo እና በተመሳሳይ የግራናይት መደብ ላይ በወርቃማ ቀለም (Golden Color) በእንግሊዘኛ እና አማርኛ የሚቀረፅ የዋና መስሪያ ቤቱን ስም የአቅርቦት እና ገጠማ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች በሞያው ያላቸውን በቂ የስራ ልምድ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት
4. ተጫራቾች የስራውን ዝርዝር ሁኔታ ለመመልከት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ጦር ሀይሎች ፊት ለፊት በምድር ሀይል ግቢ ውስጥ ባለው ቢሮአችን ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ለእቃው በዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ እና ሳይጨምር ተብሎ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ3ኮፒ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
8. ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡- ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ በሚሰራው ህንፃ ፕሮጀክት መምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118-49 38 23 ይደውሉ፡፡