የሲቪል ፈንጅ ግዥ (የተራዘመ)
የጨረታ ማራዘምን ይመለከታል፡-
ኢንተርፕራይዛችን ለበለስ መካነ ብርሃን መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የሲቪል ፈንጅ ግዥ አስመልክቶ በግልፅ ጨረታ ቁጥር DCE/OI/73/2018 ግብዣ መደረጉ እና ቴክኒካል ጨረታው ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚከፈት የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው፡-
ጨረታው፣ ሰኔ 07 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋል
ሰኔ 07 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል
ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን ከጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡