Skip to main content
x

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር (ከዚህ በኋላ ሻጭ ተብሎ ሊጠራ ይችላል) 5ኛ ደረጃ እጣን፣ለኤክስፖርት ተበጥሮ የተዘጋጀ ንፁህ አኩሪ አተርና ማሾ በተጨማሪም ሪጀክት ማሾ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የሚከተሉትን መመሪያዎች አሟልቶ የተገኘ ሰው (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት) በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር (ከዚህ በኋላ ሻጭ ተብሎ ሊጠራ ይችላል) 5ኛ ደረጃ እጣን፣ለኤክስፖርት ተበጥሮ የተዘጋጀ ንፁህ አኩሪ አተርና ማሾ በተጨማሪም ሪጀክት ማሾ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የሚከተሉትን መመሪያዎች አሟልቶ የተገኘ ሰው (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት) በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

1.    የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያመላክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና በንግድ ዘርፉ የተሰማራ ሰው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

2.    የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤

3.    TIN (የንግድ መለያ ቁጥር) ያለው እና ማቅረብ የሚችል፣

4.    ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ያቀረበውን የመጫረቻ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፣

5.    ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ ይህንን ማድረጉ የተደረሰበት ማንኛውም ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፤

6.    ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የእርሻ ውጤቶች መጠን የሚገልፅ እና የጨረታ ዋጋ መሙያ ሰነዱን ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሻጭ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ፣ ጐንደር ቅርንጫፍ ጠብቀው ህንፃ እና አምባሰል ጎንደር ኘሮሰሲንግ አገልግሎት አዘዞ ፣ ባህር ዳር አብይ ቅርንጫፍ ጣና ክፍለ ከተማ አምባሰል ሕንጻ እና ደሴ አብይ ቅርንጫፍ ሆጤ ክፍለ ከተማ መነሐሪያ ወረድ ብሎ ጅንአድ የሚገኝበት ግቢ ውስጥ ድረስ በመሄድ መግዛት ይችላሉ፤

7.    ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ የቀረበውን 5ኛ ደረጃ እጣን ባ/ዳር አብይ ቅርንጫፍ በሚገኘው የእርሻ ሰብል መጋዘን እና አኩሪ አተሩን እና ማሾውን አ/አበባ ቃሊቲ የኩባንያው መጋዘን ድረስ በአካል ሄደው በማየት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡ በአካል ተገኝቶው ያልተመለከቱ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለጨረታ የቀረቡትን የእርሻ ውጤቶች ባለበት ሁኔታ ለመግዛት እንደተስማሙ ይቆጠራል፡፡

8.    ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ (ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ያለው ጊዜ የሻጭ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል) ሲሆን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ታሽጎ የሁሉም ቅርንጫፎች የመጫረቻ ሰነዶች ተሰብስበው በ13ኛው የሥራ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ስዓት አ/አበባ የሻጭ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣

9.    ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ሻጭ ጨረታውን እንዳሸነፈ በነገረው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው በሻጭ የተዘጋጀውን የሽያጭ ውል መፈረም የሚኖርበት ሲሆን፤ ሻጭ ጨረታውን ማሸነፋ በተነገረው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ለመዋዋል ያልቻለን ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን በመውረስ እንደአስፈላጊነቱ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች የመሸጥ ወይም ጨረታውን ሰርዞ በፈለገው መንገድ የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

10.   ማንኛውም ተጫራጭ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት ለማንሳት ከሻጭ ጋር ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ በጨረታ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

11.   ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፉበትን ዕቃ ለማንሳት ውል ከተዋዋበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ንብረቱን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ዋጋቸውን ከፍሎ ማንሳት ካልቻለ ሻጭ ተጫራጩ ያስያዘውን የውለታ ማስከበሪያ በመውረስ የእርሻው ውጤት ምርቶችን በሌላ መንገድ የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቹ በውሉ አግባብ ለሽያጭ የቀረቡትን የእርሻ ውጤቶች ሙሉ ዋጋ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን ማንሳት ባይችል ሻጭ ለንብረቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

12.   ተጫራwች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን አዘጋጅተው ሲያቀርቡ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያየ ፓስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በአስተሸሸግ ችግር ምክንያት ለሚከሰት ማንኛውም አይነት የሰነድ መጥፋት ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

13.   ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ እና ሞልቶ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ካስገባ በኋላ ወይም ጨረታው ከሚከፈትበት ከ2 ቀን በፊት ራሱን ከጨረታው ማግለል አይችልም፡፡ ማንኛውም ተጫራጭ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ራሱን ከጨረታው ማግለል ከፈለገ ሻጭ የጨረታ ማስከበሪያውን መውረስ ይችላል፤

14.   ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

15.   ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-466-65-02/058-226-65-06/07/058-114-03-93/058-111-12-14/033-111-27-66/011-439-39-75  ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፤

ማሳሰቢያ፡- ድርጅታችን ቅዳሜ እስከ 6፡30 ስዓት የሚሰራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር