የተለያዩ የሰራተኞች አልባሳትና የአደጋ መከላክያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ ጨረታ ቁጥር 97/2017/18
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር የሥራ ሂደት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የሰራተኞች አልባሳት ግዥዎችን በረጂም ጊዜ በሚፈጸም ግዥ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆኑ ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይንም ቅድመ ሁኔታ ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና |
ምድብ አንድ |
|||
1. |
ሸሚዝ |
9,127በቁጥር |
60,000.00 |
ምድብ ሁለት |
|||
2 |
ቆዳ ጫማ |
4,737በጥንድ |
41,000.00 |
ምድብ ሶስት |
|||
3 |
ብትን ጨርቅ |
16,193.30 ሜትር |
81,000.00 |
ምድብ አራት |
|||
4 |
ካኪ የስራ ካፖርት |
1067 በቁጥር |
6400 |
5 |
ካፖርት ባለፈር |
420 በቁጥር |
3800 |
6 |
ቱታ |
239 በቁጥር |
3800 |
ምድብ አምስት |
|||
7 |
የዝናብ ልብስ |
918 በቁጥር |
18400 |
8 |
የአፍ መሸፈኛ |
1,061 በቁጥር |
600 |
9 |
የአደጋ መከላከያ ጫማ |
100 በጥንድ |
5000 |
ምድብ ስድስት |
|||
10 |
ቆብ |
958 በቁጥር |
2300 |
11 |
ክራቫት |
2,110 በቁጥር |
1200 |
12 |
የእግር ሹራብ |
8,902 በጥንድ |
3500 |
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃዳቸውን፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ውስጥ የተመዘገቡበትን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2010ዓ.ም ጀምሮ ዘወትርበሥራ ሰዓትከጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡00-10፡15 ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር011-3722858/47/26/78/74 በፋክስ ቁጥር 011-3691994 ዳይሬክተር ዕቃ አቅርቦት እና አስተዳደር መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት ትክክለኛ የሆነ የቀጥታ መስመር ስልክ ቁጥር፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፤ የኢሜል አድራሻ እና የፋክስ ቁጥር ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።ሆኖም ግን ማንኛውም ተጫራች ትክክለኛ አድራሻ ሳይሰጥ ቢቀር ወይም በማንኛውም ምክንያት የሰጠው አድራሻ ሳይሰራ ቀርቶ በባንኩ የተላከ ማንኛውም ዓይነት መረጃ ባይደርሰው ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ሰነዱ ውስጥ በተጠየቀው መልኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 02 ቀን 2010ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትድረስ እያስመዘገቡ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው የፍላጐት መግለጫ ዝርዝር መሠረት ምላሽ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 02ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ለመገኘት ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡