የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አዲስ ለሚሰራቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ Pick up Double Cabin vehicle ግዥ አስመልክቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/OI/174/2018
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አዲስ ለሚሰራቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ Pick up Double Cabin vehicle ግዥ አስመልክቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1 ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
3 ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔሲፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
4 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
5 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ታህሳስ 04/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6 ጨረታው ታህሳስ 04/2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7 ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ