Skip to main content
x

ዲኤኣይ አውሮፓ ከፈርስት ኮንሰልት፣ የቆዳና ሌጦ የጥራት ማሻሻያ ተሞክሮችን ለማስተዋወቅና ለማስረጽ ለሚሠራ ሥራ የተሳትፎ ጥሪ፤

የቆዳና ሌጦ የጥራት ማሻሻያ ተሞክሮችን ለማስተዋወቅና ለማስረጽ ለሚሠራ ሥራ የተሳትፎ ጥሪ፤

መነሻ፤ ዲኤኣይ አውሮፓ ከፈርስት ኮንሰልት፣ ኤንክሉድ እና ኢታድጋርበ ትብብር በእንግሊዝ መንግስት የፋይናንስ ድጋፍ የተዘረጋዉንና ኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ (ኢፒ) የተሰኘዉን 15 ሚሊዮን ፓውንድ የሰባት ዓመት የልማት ፕሮጀክት እያስተዳደረያ ለና በኢትዮጵያ መንግስት ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት እቅዶች ላይ በመመርኮዝ የግል ባለ ሀብቱን በመደገፍና ትራንስፎርም በማድረግ ላይያለመነዉ፡፡

የኢፒ የድጋፍ ስልት ቁልፍ የልማት ማነቆዎችን በመለየትና እነዚህ ማነቆዎች እንዲቀረፉ በመደገፍ የሥራ ገበያ ስሪቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች በተለይም ለሴቶች ተደራሽነትን ማስፋት (making market work for poor/all) ሲሆን፤ እነዚህ ዜጎች ከግል ዘርፉ ጋር በዘላቂነት ቁርኝት ለመፍጠር የሚያስላቸዉ ጉዳዮች ላይ በመስራት ላይ ያለ ፕሮጀክት ነዉ።

የዚህ የግብዣ ጥሪ ዓላማዉ የተመረጡ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎችን በኢፒ ድጋፍ የሙከራ ፕሮጀክት ወይም ፓይለት ላይ እንዲሳተፉ በመጋበዝና በቆዳና ሌጦ አመራረትና አያያዝ ላይ የአሥራር መስፈርትን መሰረት ያደረገ የጥራት ማሻሻያ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለጥሬ ቆዳ አምራቾች (ቄራዎች) እና ለነጋዴዎች በማስረጽ ብሎም በቆዳና ሌጦ አገፋፈፍ፣ አስተጃጀል፣ መጠን አለካክ፣ ደረጃ አሰጣጥ፣ መጋዘን አያያዝና ንጽህና አጠባበቅ፣ ፍሳሽ አወጋገድ፣ የሠራተኞች ጤንነትና ድህንነት አጠባበቅ ላይና እንዲሁም በቆዳ አቅራቢዎችና በቆዳ አልፊዎች መካከል ያለዉን ጤናማ ያልሆነና የላላ የገበያ ትስስርን በማሻሻል ዘላቂና ዉጤታማ የአቅርቦት ሰንሰለት ለመፍጠር ነዉ፡፡

በዚህ መሰረት ኢንተርፕራይዝ ፓርተነርሰ የተገቢነት መስፈርቶችን የሚያሟሉና ፍላጎት ያላቸዉን የጥሬ ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎች በዚህ የፓይለት ፕሮጀክት እንዲሳተፉ የጋበዘ ሲሆን የአመልካቾች የተገቢነት መስፈረቶች የሚያካትቱት:-የቆዳና ሌጦ ንግድን ለማከናወን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ ለቆዳና ሌጦ ማዘጋጃ የሚያመችና የፍሳሽ እና የቆሻሻ ማስወገጃ መስመሩ ከዋናዉ የቆሻሻ መስመር ጋር የተጋጠ መመጋዘን ያለዉ፣ እንዲሁም ከአካባቢ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሪፖርት የሌለበት፣ ተሰብሳቢ ክፍያቸዉን ጨምሮ የሥራ ማስኬጃ ካፒታሉ 1.5 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ያለዉ፣ በቁጥር ከሶስት ያላነሱና አሁን ላይ አብረዉት እየሰሩ ያሉ ደንበኞች (ቆዳ ፋብሪካዎች) ያለዉ፣ ቢቸል ከቄራዎች ጋር በቀጥታ እየሠራ ያለ፣ከ5 ያላነሱ ቋሚ ሠራተኞች የያዘናቢያንስ አንድ የግዥና ሽያጭንና ሌሎች መረጃዎችን የሚመዘግብ ሰራተኛ ያለዉ፣ ከገዥዎች ጋር በዘላቂነት አብሮ ለመስራት ውል ወይም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፣ የቆዳ ፋብሪካዎችን የጥራት ፍላጎት እንዳጠቃላይ የተረዳ፣ በጥራት ላይ የሚሰጥን ግብረ መልስ ለመቀበል ዝግጁ የሆነና ፈጥኖ ለማረም ተነሳሽነቱና ቁርጠኝነቱ ያለዉ፣ የተሻሻለዉን የቆዳና ሌጦ አዋጅ ቁጥር 1073/2018 አጠቃላይ ይዘት የተረዳና በዚህ አዉድ መሰረት ለመስራት ዕውቀትና ቀዳሚ ተነሳሽነት ያለዉ፣ በጥሬ ቆዳና ሌጦ ደረጃ አሰጣጥ ላይ የሀገሪቱና የኢንዱስትሪውን ደረጃ አሠጣጥ ግንዛቤ ያለዉ፣ የተሻለ የዉስጥ አሠራርን በመከተልና በተለይ በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ የሚከሰቱትን የጥራት ግድፈቶች በመቆጣጣር የቆዳና ሌጦ ጥራት ደረጃን ማሻሻል እንደሚቻ እምነቱና ቁርጠኘነቱ ያለዉ የሚሉትን ያካትታል፡፡ 

በዚህ መሰረት  ፍላጎቱ ያላቸዉ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎች በዚህ ፕሮጅት ለመሳተፍ 10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በጽሁፍ (በአካል በኢሜል ወይም በፖስታ)ማመልከት የሚችሉና ለዚህ ሥራ የተዘጋጀዉን ዝርዝር ቢጋር መዉሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልጸለን፡፡

አድራሻችን፡-

ዩሮፕ/ኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ፡-

ኢሜል፡[email protected]

Addis Ababa, WelloSefer, Kas Building 12thfloor. Tel. +251-114701474/ 0114702259

..ቁ፡-27374/1000