ወጋገን ባንክ አ.ማ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር ወጋገን 03/2011
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ
የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛውን ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሠነድ (C.P.O) በማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት ቀናት/ ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወድያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ/አድራሻ ፡
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ብቻ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከባንኩ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ቤቶቹን መጎብኘት ይችላል፡፡
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች እና ባለንብረቶች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ በሙሉ የጨረታ አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ወጋገን ባንክ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 0118-78-76-26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ወጋገን ባንክ አ.ማ