Skip to main content
x

በኦፕሬተርነት ለማስተዳደር የመቀሌ ኖክ ነዳጅ ማደያን

 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመቀ ኖክ ነዳጅ ማደያን በኦፕሬተርነት ለማስተዳደር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) በሃገራችን የፔትሮልየም ውጤቶች ገበያ ዘርፍ የመሪነቱን ስፍራ የጨበጠና በአይነታቸውም ዘመናዊ እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ የሆኑ የነዳጅ ጣቢያዎችን ለነዳጅ ስርጭት አመቺ በሆኑ የተለያዩ የሃገሪቱ ስፍራዎች ላይ በመገንባት ለህብረተሰቡ ጥቅም በማቅረብ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ብቁ ከሆኑ የማደያ ኦፕሬተሮች /ወኪሎች/ ጋር በጋራ ይሰራል፡፡

ድርጅታችን በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀብነት ክፍለ ከተማ መስተዳድር በፈጣን የእድገት ጎዳና በምትገኘው መቀ ከተማ ላይ ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለከተማዋና አካባቢዋ ህብረተሰብ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ያደረገ መሆኑን በደስታ እያበሰረ፣ ይህን የኖክ ነዳጅ ማደያ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ፍላጎቱና ብቃቱ ያለው/ያላት ግለሰብ በወኪል ኦፕሬተርነት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ማደያ ጣቢያው የመኪና እጥበት አገልግሎት እንዲሁም ለዘይት እና ቅባት መሸጫ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች እና  ምድር ቤት እንዲኖሩት ሆኖ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ በኖክ ዋናው መስሪያ ቤት 2ተኛ ፎቅ ሪቴይል ሸያጭ ክፍል በግንባር ቀርቦ በመውሰድ እና በመሙላት ስራውን ለማከናወን የሚችሉ መሆኑን ከሚያሳዩ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለኩባንያው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ .የተ.የግ .(ኖክ)

የሪቴይል ማርኬቲንግ ክፍል - 011-662-2907 ይደውሉ፡፡