Skip to main content
x

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)…በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎችን የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ

የጨረታ  ማስታወቂያ

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (..) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን /የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1.    የመኪኖቹን/የንብረቶቹን ሁኔታማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪን ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት በመገኘት ከየካቲትቀን 2012  .. ጀምሮ ማየት ይችላሉ፡፡

2.    ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው አዲሱ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና /ቤት ካሣ መምሪያ አንደኛ ፎቅ ከየካቲትቀን 2012  .. ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.    ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 13   ቀን 2012  .. እስከ  1100 ሰዓት ድረስ ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና /ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.    ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታታማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያዣነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲÁውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

5.    ጨረታው የካቲት 14  ቀን 2012  .. ከጠዋቱ 300 ሰዓት ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፊታል፡፡

6.    ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ 5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ 10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሀያ ቀናት በየቀኑ ብር 30.00 /ሰላሳ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡

7.    ለጨረታታከቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለG ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡

8.    ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-352283 ወይም 0116187000/6632947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡

9.    መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10.   ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡

11.   ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

12.   ጨረታው በተመለከተ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

13.   ተጫራጮች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወደ ስማቸው ለማዞር ከተሸጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ወደ ስማቸው ማዞር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ኩባንያው በተሽከርካሪው ላይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር እና ለሚደርሰው ጉዳት ኩባንያው ሃላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን፡፡

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (.)